Tuesday, 18 September 2012
The ten commandments
ክርስቲያናዊ ሥነ - ምግባር
አሥርቱ ትዕዛዛት
ከእግዚአብሔር አምላክ በቀጥታ በሙሴ አማካኝነት ለእስራኤላውያን የተሰጠ ሕግ ነው፡፡ የተሰጡትም እስራኤላውያን ከግብጽ ከወጡ በ3ኛው ወር ፋሲካን ካከበሩ
በ3ኛው ቀን በደብረ ሲና ሰፍረው ሳለ ነበር፡፡ ዘፀ. 19፡1-4
በዘዳ. 34፡28 ዘዳ. 4፡13 ላይ አሥሩ ትዕዛዛት አሥር መሆናቸውን እንረዳለን፡፡
በዝርዝር ተጽፈው የሚገኙት ግን በዘዳ. 20፡ 3 እና17 ዘዳ. 5፡5-21 ላይ ነው፡፡ አሥርቱ ቃላትና ስድስቱ ቃላተ ወንጌል ለእስራኤል ዘስጋና ለእስራኤል ዘነፍስ የተዘጋጁ
ስለሆነ ሁላችንንም ይመለከታል፡፡ እነርሱም፡-
1. ‹‹ እግዚአብሔር አምላክህ እኔ ነኝ፡፡ ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ የማናቸውንም ምሳሌ የተቀረጸውን
ምስል ለአንተ አታድርግ፤ አትስገድላቸው፤ አታምልካቸው ››ዘፀ. 20፡2-6
2. ‹‹ የእግዚአብሔር የአምላክን ስም በከንቱ አትጥራ፡፡ ››ዘፀ. 20፡7
3. ‹‹ የሰንበትን ቀን ትቀድሰው ዘንድ አስብ /አክብረውም/›› ዘፀ. 20፡ 8
4. ‹‹አባትህንና እናትህን አክብር››ዘዳ.20፡12
5. ‹‹ አትግደል ›› ዘፀ. 20፡13
6. ‹‹ አታመንዝር ›› ዘፀ. 20፡14
7. ‹‹ አትስረቅ ›› ዘፀ. 20፡15
8. ‹‹ በሐሰት አትመስክር ›› ዘፀ. 20፡16
9. ‹‹ አትመኝ ›› ዘፀ. 20፡17
10. ‹‹ ባልንጀራህን እንደ ራስህ ውደድ ›› ዘሌ. 19፡18
- አሥርቱ ሕግጋት የብሉይ ኪዳን መሠረቶች ናቸው፡፡የእግዚአብሔርን ሕግ ብትጠብቁ ብትፈጽሙትም ሕዝቤ
ትሆናላችሁ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ ብሎ ቃልኪዳን ገባ፡፡
ሕዝቡም በአንድ አፍ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው
‹‹እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እናደርጋለን እንታዘዛለን››ብለው ቃል ኪዳን ገቡ፡፡ ዘፀ. 19፡8፤ 24፡1-8 ቅዱስ ጳውሎስም እንደነገረን ይህ ፊተኛው ኪዳን ያለ ደም
አልተመረቀምና ዕብ. 18፡ 22 ሙሴ ኪዳኑን ለማጽናት የደም መርጨትን ሥርዓት እንዳደረገ በሐዲስ ኪዳንም ቢሆን
ሥነ ሥርዐቱ ሙሉ በሙሉ ተቀባይነት ያላቸው ሕግጋት ናቸው፡፡ ማቴ 5፡17፣ 19፡15-22 ፣ዮሐ1፡12
እግዚአብሔር ሕዝቦቹና ልጆቹ ሊያረገን ይህን ታላቅ ተስፋ በመስጠት ቃል ከገባልን እኛ ደግሞ ትዕዛዙን ለመጠበቅ ምን
ያህል ቃል ገብተንለታል? ጌታችን ብትወዱኝስ ትዕዛዜን ጠብቁ ዮሐ 14፡15 እንዲሁም ከሆነ እንደ እስራኤላውያን
እግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እናደርጋለን እንታዘዛለን ብለንከሁሉ በፊት ለእግዚአብሔር ቃል መግባት አለብን፡፡ክርስትናውን ስንጀምር የመጀመርያ ሥራችን መሆን ያለበትይህ ነው፡፡
የዐሥርቱ ትዕዛዛት ዓላማ
ዐሥርቱ ትዕዛዛት የተሰጡት በሚከተሉት ዓላማዎች ነው፡፡ይኸውም፡-
1. ከግብጽ ምድር ስላወጣቸው ውለታውን እንዲያስቡ
2. ወደ ፊት በአረማዊያን መካከል ሲመላለሱ ከኃጢአት እንዲቆጠቡ
3. መንፈሳዊ አካሄዳቸው ምን ምን አቅጣጫ መከተል እንዳለበት ለማሳየት ነው፡፡
Subscribe to:
Post Comments (Atom)
No comments:
Post a Comment